ኢትዮጵያ ፊቷን ወደ ጠፈር ሳይንስ እያዞረች ነው

ባህር ዳር ፡ነሀሴ 21/2007 ዓ/ም (አብመድ) 3200 ሜትሮች ከፍታ ባለው የእንጦጦ ተራራ ላይ በግማሽ ክብ ቅርጽ በተገነባው የብረት ሕንጻ ውስጥ አንድ ሜትር ስፋት ያላቸው ቴሌስኮፖች መተከላቸው ኢትዮጵያ የጠፈር መርሃ ግብር በማካሄድ ከጥቂት የአፍሪካ ሀገራት አንዷ መሆኗን እንደሚያመላክት አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ገለጸ፡፡

‹‹ሳይንስ የልማት አካል ነው ፡፡ሳይንስና ቴክኖሎጂ በሌለበት ስኬት አይታሰብም ፡፡የኛ ቀዳሚ ተግባር ወጣቱ ትውልድ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተሳታፊ እንዲሆን ማብቃት ነው››ያሉት የኢትዮጵያ የጠፈር ሳይንስ ማህበር ቃል አቀባይ አብነት እዝራ ማህበሩ እ.ኤ.አ.በ2004 በኢትዮጵያዊው ባለሃብት ሼክ ሞሃመድ አላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ ሲመሰረት የስነፈለክን ጥናት ለማስተዋወቅ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

ባለፉት ጥቂት አመታት የጠፈር ምርምር ጣቢያው ዳይሬክተር እና የአስትሮ ፊዚክስ ባለሙያ የሆኑትን ዶክተር ሰለሞን በላይን ጨምሮ እፍኝ የማይሞሉ የሙያው አጋሮች ከሚመለከታቸው የመንግስት ሃላፊዎች ጋር በመደራደር መርሃግብሩ እውን እንዲሆን የበኩላቸውን ያልተቆጠበ ጥረት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ምንም እንኳ የጠፈር ምርምር ጣቢያው የሚገኝበት እንጦጦ በክረምት ወራት ደመናማ ከመሆኑ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ መብራት በቅርብ መገኘት ከደቡብ አፍሪካው ግዙፍ ክልላዊ ቴሌስኮፕ እና ከሌላው አለም ጣቢያዎች ጋር ተፎካካሪ እንዳይሆን እንቅፋት መፍጠሩ አይቀርም ቢባልም ለክልሉ ግን ትልቅ ተምሳሌት ከመሆን አላገደውም፡፡

የዜና ምንጩ አያይዞ እንደገለጸው ከከተማ መብራቶች በራቁ አካባቢዎች ጠንካራ አቅም ያላቸው ትላልቅ የጠፈር መመልከቻ ጣበያዎች ለማቋቋም ኢትዮጵያ ስታቅድ ከነዚህ ውስጥ በሰሜናዊ ተራሮች መካከል የሚገኘው የላሊበላ አካባቢ አንዱ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ብሄራዊ የጠፈር ኤጀንሲ ለማቋቋም ያሰበ መሆኑ ሲገለጽ ኮሙኒኬሽንን ለማቀላጠፍ እና የእርሻ ማሳዎችን ለመቆጣጠር በቀጣዮቹ አምስት አመታት ውስጥ ሳተላይት ወደ ጠፈር የማምጠቅ 
ፍላጎት እንዳለው ዘገባው አመላክቷል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ የአለም አቀፍ ስነፈለክ ማህበር ሃላፊ ከላሊ አድሃና ሲናገሩ ‹‹ዛሬ በሁሉም መስኮች የጠፈር ቴክኖሎጂ እየተጠቀምን ነው፤ለተንቀሳቃሽ ስልክ ፡ለአየር ንብረት ክትትልና ለሌሎች በርካታ ተግባራት በመሰረታዊነት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ይህ ዘርፍ ነው ››ብለዋል፡፡

በአማራ ቴሌቪዥን ፣በአማራ ራዲዮ እና በኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 ዜናዎች እና ዝግጅቶች ዙሪያ ለሚኖርዎት ጥቆማና አስተያየት ለአማራ ቴሌቪዥን(ATVን)፣ ለአማራ ራዲዮ(ARን) እና ለኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 (FMን) በማስቀደም በ8200 ማድረስ ይችላሉ፡፡
#intechcompany via #ATV news!

for more news and tech like,follow and subscribe our pages.
thanks!! 
click on the facebook page link and like it.
https://www.facebook.com/pages/INTECHCOMPANY/405384176293840

No comments

intech company. Powered by Blogger.